በኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ” ተስፋን እንትከል ” በሚል መሪ ቃል የወረዳው አመራሮች እና ባለሙያዎች በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በጋዳ ጋሪ ቀበሌ ሚሊንየም ፓርክ ተገኝተው አሻራቸውን አሳርፈዋል። በተከላ መርሐ- ግብሩ የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማላ ማዴሶ እንዳሉት የአሪንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥ ከመቆጣጠር ረገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን በማንሳት ትውልድ ችግኝ ከመትከል ባሻገር በእንክብካቤ መያዝም እንደሚገባ ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች እንደ ሀገር መተከሉን አንስተዉ ዘንድሮም የአፈርና የውሃ ሀብትን ለመጠበቅ፣ የጥምር ግብርናን ለማስፋፋት፣ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር እና የማህበረሰቡን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ችግኞች በተመረጡ ቦታዎች በ93 ሄ/ር መሬት ለ8ኛ ዙር እየተከናወነ አንደሆነ አቶ ማላ አያይዘው ገልፀዋል። ከዚህ መነሻ ነገን ዛሬ በመትከልና ለቀጣይ ትውልድ ታሪካዊ አሻራችንን በማሳረፍ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም እንደሚገባም ዋና አስተዳዳሪው ጠቁመዋል። ዛሬ ላይ የሚናሳርፈዉ አሻራ ለነገ ታሪክ መሰረት ነዉ ያሉት አቶ ማላ ህብረተሰቡ ተጠናክሮ ያለዉን ችግኝን መንከባከብ ባህል በማጠናከር ለታለመለት ዓላማ እንዲዉል ማድረግ እንደሚጠበቅም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የወረዳው ግ/አከ/ጥ/ህ/ስ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን አበበ አረንጓዴ አሻራ የአፈር ለምነትን በመጠበቅና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ከፍ ያለ አስተዋጽኦ እንዳለው በማንሳት እንደ ወረዳ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በአንድ ጀንበር 202,954 በተመረጡ በ12 ሳይቶች ከ11,907 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ እየተከናወነ እየተከናውን ገልጿል።በመረሃ-ግብሩ የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማላ ማዴሶን ጨምሮ የወረዳው አስፈፃምዎች እና የዞኑ ደጋፊ አመራሮች እንዲሁም ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።ዘገባው የኤላ ሀንቻኖ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።