የኮንታ ዞን በአዲስ መልክ ወደ ዞን ከፍታ ከማደጉ በፊት የልዩ ወረዳነት መዋቅር ያገኘው በቀድሞ ደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ውስጥ በነበረበት ወቅት በህዳር 1993 ዓ/ም ሲሆን ዕዉቅና አግኝቶ ወደ ዞን መዋቅር ያደገው በአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት መስራች ጉባኤ ህዳር 14/2014 ዓ/ም ነዉ፡፡

የኮንታ ዞን በ6.46’-7.26’ ሴሜን ላቲቲዩድ’’ እና በ36.32-36.87 ምስራቅ “ሎንግቲዩድ” መሥመሮች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በስተ ሰሜን በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከጅማ ዞን ዴዶ እና ማንቾ ወረዳ፣በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በከፋ ዞን በስተምዕራብ ጨታ፣ ዴቻ፣ ጠሎና አዲዮ ወረዳ፣ በምሥራቅ ከዳውሮ ዞን ታርጫ ዙሪያ፣ ቶጫ፣ ኢሰራ ወረዳ፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በደቡብ ኦሞ ዞን ከሰላማጎ ወረዳና በስተደቡብ ምሥራቅ ከጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ያዋስኑታል፡፡ ዞኑ በሦስት ወረዳ እና በሁለት ከተማ አስተዳደር የተዋቀረ ሲሆን በእነዚህም መዋቅሮች አምስት ማዘጋጃ ቤት፣17 ከተማ ቀበሌዎችና እና 45 የገጠር ቀበሌዎች በድምሩ 62 ቀበሌዎች ይገኛሉ።

የዞኑ ዋና ከተማ አመያ ስትሆን ከዋና ከተማ መነሻ አንስቶ ከሀገሪቱ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ- ጅማ አመያ 465 ኪ/ሜ፣ ቦንጋ-ጅማ-አመያ በኩል 225 ኪ/ሜ ሲሆን ቦንጋ-ፈለገ ሰላም-አመያ 109 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች። የዞኑ ቆዳ ስፋት 2,381.63 ስኩዌር ኪሎ ሜትር (238,163 ሄ/ር) ሲሆን ከዚህ ውስጥ 89,370.67 ሄ/ር (37.525%) መሬት በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ደን የተሸፈነ ነው፡፡ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጡ 28% ሜዳማ፣ 38.5% ተራራማ እና 33.5% ተዳፋታማ ነው።

ዞኑ በቋሚ ሰብል የተሸፈነ 26,463 ሄ/ር እና በዓመታዊ ሰብል የተሸፈነ 77,362 ሄ/ር በድምሩ 103,825 ሄ/ር (43.6%) የለማ መሬት ያለው ሲሆን ለግጦሽ የተከለለ መሬት 3,893 ሄ/ር፣ ወደ ፊት ሊለማ የሚችል 12,981.46 ሄ/ር፣ ወደፊት ሊለማ የማይችል 417.6 ሄ/ር፣ በግንባታ የተከለለ (የተያዘ) 3,991 ሄ/ር፣ በቁጥቋጦ የተሸፈነ 11,121.4 ሄ/ር፣ በዉሃ የተሸፈነ 1,050 ሄ/ር፣ ቦረቦር መሬት 1014.45 ሄ/ር እና ረግረጋማ መሬት 317.16 ሄ/ር መሬት አለው፡፡ ዞኑ በ4 የአግሮ ኢኮሎጂ ቀጠናዎች የሚከፈል ሲሆን በረሃ 18.58 ሄ/ር (0.0078%)፣ ቆላ 182,051.7972 ሄ/ር (76.44%)፣ ወይና ደጋ 54,539.33 ሄ/ር (22.9%) እና ደጋ 1,553.2828 ሄ/ር (0.65%) ነው፡፡

ዞኑ የበልግና የመኸር ዝናብ ተጠቃሚ ሲሆን ከፍተኛው የዝናብ መጠን 2,290 ሚ.ሜ እና ዝቅተኛው 1,200 ሚ.ሜ ሆኖ አማካይ የዝናብ መጠን 1,745 ሚ.ሜ ነዉ። (SWEPRS Population projection 2015 EFY) እንደሚያሳየው አጠቃላይ የዞኑ ህዝብ ብዛት 141‚656 ቢሆንም አሁን ባለዉ የዞኑ ተጨባጭ መረጃ አጠቃላይ የህዝብ ብዛት 233‚064 ሲሆን ወንድ 114‚953 ሴት 118‚111 ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ በከተማ የሚኖረው ጠቅላላ ህዝብ 43,200 ሲሆን ወንድ 21,101፣ ሴት 22,099 እንዲሁም በገጠር የሚኖረው ህዝብ በድምር 189,864 ሲሆን ወንድ 94,322 ሴት 95,542 ነው፡፡ ዓመታዊ የሕዝብ ዕድገት በ1999 ዓ.ም በተደረገው ህዝብና ቤት ቆጠራ መረጃ መሰረት 2.9% ሲሆን ከጠቅላላው ሕብረተሰብ ውስጥ በአምራች ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ (ከ15-64) ዓመት ያለው 50.9% (112,122) ሲሆን አምራች ባልሆነ ዕድሜ ክልል ውስጥ (ከ15 ዓመት በታች እና ከ64 ዓመት በላይ) የሚገኘው ሕዝብ 49.1% (108,157) ነው።

በዚህም መሰረት አማካይ የቤተሰብ አባላት ቁጥር 4.9 እንደሆነ ይገመታል። ከጠቅላላ የዞኑ ሕዝብ ውስጥ 18.5% የሚሆነው በከተማ የሚኖር ሲሆን 81.5% ህዝብ የሚኖረው በገጠር ነው፡፡ ዞኑ የተለያዩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች የሚኖሩበት አካባቢ ሲሆን በዋናነት ነባሩ የኮንታ ብሔረሰብ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ በተጨማሪም የዳዉሮ፣ የካፋ፣ የኦሮሞ፣ የአማራ እና ሌሎችም ብሔረሰብ አባላት ከረዥም ጊዜ አንስቶ ከነባሩ ብሔረሰብ ጋር በሠላምና በፍቅር ይኖራሉ፡፡ መንግስት የገጠሩን ማህበረሰብ የምግብ ዋስትና ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በነደፈዉ የሰፈራ ፕሮግራም ከወላይታ እና ከሀዲያ አካባቢዎች የመጡ የወላይታ እና ሀዲያ ብሔረሰብ ተወላጆች በዞኑ በኮንታ ኮይሻ ወረዳ ውስጥ ሰፍረዉ ይገኛሉ፡፡ ይህም ኮንታን የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች አብረው ተቻችለው የሚኖሩባት ትንሿ ኢትዮጵያ ያደርጋታል፡፡