በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር የተቀናጀ የጤና (TELCOM+ Campaign) ዘመቻ በአመያ 03 ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል። ዘመቻውን በይፋ ያስጀመሩት የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ኡቴ አየለ እንደገለጹት በየጊዜው በህብረተሰቡ ውስጥ የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመከላከል በዘመቻ የሚሰጡ ክትባት እና መድኃኒት ዕድላ በጥንቃቄና በአግባቡ ማደል እንደሚገባ አሳስበዋል ። የተቀናጀ የጤና ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ማህበረሰቡ መተባበር እንዳለባቸው ያሳሰቡት መምሪያው ኃላፊ በኦንኮ መድሃኒት እደላ ዘመቻ በከተማው በታቀደው ዕቅድ መሰረት ተደራሽ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በልዩ ቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።አክለውም የኦንኮሰርኪያሲስ በሽታ “ኦንኮ-ሰርካ” በሚባል ጥገኛ ተህዋስ የሚከሰትና ከሰው ወደ ሰው በፈጣን ወራጅ ወንዝ በሚራቡ ጥቁር ዝንቦች ንክሻ አማካኝነት የሚተላለፍ በሽታ መሆኑን አስረድተዋል።
የከተማው ጤና ዩኒት አስተባባሪ አቶ ማሞ መሰለ በበኩላቸው በሽታዎችን መከላከል፣ ህክምና እና የመድኃኒት ዕደላ ዘመቻ ላይ ለጤና ባለሙያዎችና ለጤና ኤክስቴንሽኖች በቂ ግንዛቤ ተፈጥሮ ወደ ዘመቻ መገባቱን ገልጸዋል።አክለውም አቶ ማሞ ተገቢውን የመድኃኒት ዕድላ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በላይ ለሆኑ ለማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን ማስቻልና የተያዘውን ዕቅድ ማሳካት ከምንም በላይ ልሆን ይገባል ስሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በማስጀመሪያ መረሃ ግብሩም የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ኡቴ አየለ፣ የኮንታና ዳውሮ ዞኖች የካርተር ሴንተር ኢት/ያ የተቀናጀ ኦንኮ ማጥፊያ አስተባባሪ አቶ ባሳ በተላ፣ የከተማ አስተዳደር የጤና ዩኒት አስተባባሪ አቶ ማሞ መሰለን ጨምሮ ሌሎች የቀበሌ ጤና ባለሙያዎች ተገኝተዋል። ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።


