ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዉስጥ 80% የሚሆነዉ ለሀገራችን ኢኮኖሚ መሠረት በሆነዉ በግብርና ዘርፍ ይተዳደራል፡፡ ከጠቅላላዉ የሀገሪቱ ምርት ዉስጥ (GDP-Growth Domestic Prod uct) ግብርና ወደ 44 በመቶ ድርሻ ያለው ሲሆን በኢንዱስትሪ ጥሬ ምርት አቅርቦት ረገድም ከፍተኛውን አስተዋጽኦ ከማበርከቱም አልፎ ለኢንዱስትሪ ግብዓት ወደ ውጭ ሀገር ገበያ ከሚላኩ (Agricultural Commodities) 90% የገቢ ድርሻ የሚያስገኙትም የዚሁ ዘርፍ ምርቶች ናቸው፡፡ ከግብርና ምርቶች ወደ ውጪ ተልከው የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙት ውስጥ ቡና የመጀመሪያውን ደረጃ ሲይዝ የቅባት እህሎች፣ ቆዳና ሌጦ እንዲሁም አበባ ይከተላሉ፡፡ በመሆኑም በዞኑ ለዚሁ ዘርፍ ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮችን የያዘ ለም መሬት እና እምቅ የተፈጥሮ ፀጋ ባለቤት በመሆኑ በተለይ በቡና፣ ፍራፍሬ፣ ሰብል ምርት፣ በእንስሳት እርባታ፣ በቅባት እህሎች እና በቅመማቅመም ዘርፍ ኢንቨስተሮች ቢሳተፉ ለሀገራችን፣ ለክልላችን እንዲሁም ለዞናችንና ለራሳቸው የመጠቀም ዕድሉ የሰፋ ነው፡፡

በአካባቢዉ የግብርና ምርት አመራረት ዘይቤው ባሕላዊና ኋላቀር በመሆኑ ይህንን ባሕላዊና ኋላቀር የሆነውን የአመራረት ዘይቤ በመለወጥ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ልማት ለማረጋገጥ መንግሥት ለግብርናው ዘርፍ ቅድሚያ በመስጠት ግብርናና ገጠር ልማትን ማዕከል ያደረገ ግብርና መር የኢንዱስትሪ ልማት ነድፎ ቀጣይነት ያለዉ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ ኢንቨስተሮችን በግብርና ልማት ዘርፍ በሰፊው ለማሳተፍ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ ዞኑ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ካሉት እምቅ የተፈጥሮ ሀብት አንፃር በዘርፉ የተሰማሩ ዉስን በመሆናቸዉ ተጠቃሚ መሆን ያልተቻለ እንደመሆኑ መጠን ቀጣይ ያለዉን ሰፊ የተፈጥሮ ፀጋ ለኢንቨስተሮች ክፍት በማድረግ ይህንን እድገት በዘላቂነት ለማስቀጠል ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ናቸዉ፡፡ የመልማት አቅምና ምቹ ሁኔታዎች የመልማት አቅምና ምቹ ሁኔታዎች በዞኑ ለፍራፍሬ ሰብል ልማት ተስማሚ የአየር ፀባይ እና ሥነ-ምህዳር፣ ሰፊ መሬት፣ በዘርፉ የሰለጠነ ባለሙያና ማልማት የሚችል ልምድ ያለዉ አርሶ አደር መኖሩ በፍራፍሬ ልማት ሥራ በሙሉ አቅም ወደ ሥራ መግባት የሚያስችል ሲሆን ለዚሁ ዘርፍ ከ28 ሺህ ሄ/ር በላይ መሬት ተዘጋጅቶ ኢንቨስተሮችን በመጠባበቅ ላይ ያለ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ከ8ሺህ ሄ/ር በላይ በሚሆን ቦታ ላይ ባለሀብቶች በማልማት ላይ ሲገኙ ቀሪዉ በዘርፉ ለመሰማራት የሚፈልጉ ባለሃብቶችን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡

ኢኮኖሚ ኢኮኖሚ ግብርናችን ግብርናችን ሌላዉ የሰብል ልማት በዞኑ በእርሻ ልማት ዘርፍ የምግብ ዋስትናን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥ የኤክስፖርት ምርቶችን ለማሳደግና የኢንዱስትሪ ግብዓት ፍላጎትን ለማሟላት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት በመሆኑ በዋናነት በአነስተኛ አርሶ አደር ማሳ ላይ የሚያተኩር ሆኖ ለኢንቨስትመንት ዘርፍ ሰፊ ትኩረት በመስጠት የግል ባለሀብቱን ተሳትፎ እንዲጨምር ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት የሰብል ልማት ሥራዎችን በቅባት በብርዕ እና በጥራጥሬ ሰብሎች በመክፈል ለኢንቨስተሮች ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ግንዛቤ በማስጨበጥ ቀጣይ የግሉ ዘርፍ በሰፊው እንዲሳተፍ የዞኑ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን የቅባት እህሎች በአብዛኛው ጊዜ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኙ እንደመሆናቸው መጠን በዞኑ የሚመረቱ የቅባት ሰብሎች አማካይ የምርት መጠን በሄክታር ሰሊጥ 8.1 እና ለዉዝ 8 ኩ/ል ማምረት የሚያስችል የአየር ንብረትና ከ4,382 ሄ/ር በላይ የመሬት ዝግጅት በዞኑ መንግስት በኩል የተጠናቀቀ በመሆኑ በልማቱ ለመሳተፍ የሚመጣ ባለሀብት ያለ አንዳች እንከን ውጤታማ እንደሚሆን ዞኑ ከተለያዩ የምርምር ማዕከላት ጋር በዘርፉ የተደረገ ሰርቶ ማሳያ አማካይ ውጤት ያረጋግጣል፡፡

በተጨማሪም የጥራጥሬ ልማት በዞኑ የበልግና መኸር ምርት ወቅትን ጠብቆ እየለማ ያለ ሲሆን በዚሁ ዘርፍ ለመሰማራት ለሚፈልጉት ከ13,794 ሄ/ር መሬት በላይ ተዘጋጅቷል፡፡ በብርዕ ሰብሎች ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስና ሩዝ በሁሉም ሰብሎች ምርት የመስጠት አቅም በአማካይ ጤፍ 18፣ ስንዴ 54፣ ገብስ 22፣ ሩዝ 43 ኩ/ል ምርት በሄ/ር በበልግና መኸር የምርት ወቅት ማምረት የሚቻል ሲሆን በዘርፉ ለሚሰማሩት 15,212 ሄ/ር እና በአገዳ ሰብሎች ምርት ቅመራ የተገኘ አማካይ የምርታማነት መጠን በሄክታር በቆሎ 80-108 ኩ/ል ምርት መሰብሰብ የሚያስችል አቅም ያለዉ ነዉ፡፡ በዘርፉ መሳተፍ ለሚፈልጉ 13,544 ሄ/ር መሬት ሥነ-ምህዳርን ያገናዘበና ለዚሁ ልማት አመቺ የሆነ መሬት በመዘጋጀቱ ለራሳቸው ተጠቅመው ዞኑንም እንዲጠቅሙ በትኩረት እየተሰራ ነዉ፡፡ በተጨማሪም ዞኑ ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት ክምችት ያለው ሲሆን አብዛኛው ህ/ሰብም በዚህ ዘርፍ የሚሳተፍና የካበተ ልምድ ያለዉ መሆኑና ተፈጥሮ የለገሰው ምቹ ሁኔታ መኖሩ ከፍተኛ ዕድል ሆኖ በዘርፉ የተገነቡ ተቋማዊ አቅሞችን፣ በመጠቀም ለተቋሙ ከተሰጠዉ ልዩ ትኩረት የተሠሩ ዋና ዋና ተግባራትና የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመር ለማስፋት በሚያስችል አግባብ በዘርፉ ከፍተኛ ሥራ እየተሠራ ይገኛል ፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት • ዳልጋ ከብት ብዛት 285,314 • አነስተኛ አመንዣኪ 137,461 • ዶሮ ብዛት 340,225 • የጋማ ከብት ብዛት 15,171 • የንብ ቤተሰብ በዛት 193,455 ይገኛል ፡፡ በዘህም መሠረት ለእንስሳት እርባታ ምቹ የአየር ፀባይና እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ከመኖሩም ባሻገር በዓሳ ሀብት ልማት ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ሐይቆችና ትላልቅ ወንዞች ዉስጥ አንባዛና ቆሮሶ እንዲሁም የተለያዩ ዝርያዎች ስለሚገኙ የዓሳ ጫጩት በማልማት ከራስ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ አልፎ ለገበያ በማቅረብ መጠቀም የሚቻል ሲሆን አሁን ያለዉን ምቹ ሁኔታ እና ሰፊ የገበያ ዕድል በመጠቀም ዘርፉን በማዘመን ሁሉ አቀፍ እድገት ማስመዘገብ ይቻላል፡፡